Community empowerment (SBCC) on LLINS utilization

A four-day community mobilization and behavior change Activities for malaria prevention was conducted in Boloso Bombe Woreda, Wolaita Zone, from September 01, 2025. The initiative was a joint effort by the Federal Ministry of Health, the Southern Ethiopia Regional Health Bureau, and the Wolaita Zone Health Department.

A stakeholder meeting at the Woreda Health Office confirmed the distribution of over 25,988 long-lasting insecticidal nets (LLINs) to household heads from a total stock of 59,600 nets. The campaign disseminated crucial health messages across 20 kebeles in markets, public spaces, and roadsides.

The Roadshow emphasized several key malaria control strategies:

  • Proper and consistent use of LLINs.
  • Environmental management and elimination of mosquito breeding sites.
  • Participation in Indoor Residual Spraying (IRS).
  • Seeking immediate treatment upon symptom onset.
  • Completing the full course of medication without sharing.

This effort successfully reached over 170,000 people, including residents from neighboring Woredas, with vital information for malaria prevention and elimination.

በደቡብ ኢትዮዽያ ክልላዊ መንግስት፤ በወላይታ ዞን፤ ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ፤ ወባን ለመከላከል  የአጎበር አጠቃቀምን ለማሻሻል፤ የማህበረሰብ ንቅናቄና  የቅስቀሳ ስራ፣ የወባ ማስወገድና ህብረተሰብ ጤና ልማት ማህበር (MECHDA)፤ ከፌዴራል የጤና ሚኒስተር እና ከክልሉ ጤና ቢሮ እድሁም ከወላይታ ዞንጤና መምሪያ  ጋር በመተባባር ከ26/12/2017 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡ የንቅናቄዉን ስራ ዉጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ማለትም የዞን ጤና መምሪያ፣ የማህበሩ  እንድሁ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት  ተወካዮች ባሉበት የምክክር ሰብሰባ በቦሎሶ ቦምቤ  ወረዳ ጤና ጽ/ቤት  ተካሂዷል፡፡ በወቅቱ በወረደዉ 59,600 አጎበር ከ25,988 በላይ ለሚሆን አባወራ ስርጭት ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በቅስቀሳ ስራዉ ህብረተሰቡ መቆጣጠሪያ ስትራቴጂዎችን በተገቢዉ እንዲተገብሩ፤ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራዎ፣ አጎበር በአግባቡ እንዲጠቀም፣ የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን እንዲያፋስሱ፣ የቤት ውስጥ የፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል እንዲያስረጩ፣ የወባ ህመም ምልክቶች ሲታዩ ወድያዉኑ በአቅራቢያቸዉ ወደሚገኝ የጤና ድርጅት ሄደዉ እንድታከሙ፤ የተሰጣቸዉን መድኃኒት ለማንም ሳይሰጡ ወይም ሳያጋሩ በትዕዛዙ መሠረት ጨርሰው እንድወስዱ፤ በ20 ቀበሊያቶች፤ በገበያ ፣በህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችና በመንገድ ዳር መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ በንቅናቄ ዘመቻዉ አጎራባች ወረዳን ጨምሮ ከ170,000 በላይ ህዝብ የወባ በሽታን፤ለመከለከል፤ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት በሚያገለግሉ ቁልፍ መልዕክቶች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

Scroll to Top